Niet blij met je aankoop? Geeft niet! Je kunt artikelen tot 30 dagen retourneren
Met een cadeaubon zit je altijd goed. De ontvanger kan de cadeaubon voor alles uit ons assortiment inwisselen.
Tot 30 dagen retourrecht
ይኽ ልብስ የምድር ሰው የሠራው አልነበረም። እመቤታችንም ከልጇ መዝገብ የመጣ መኾኑን ገልጻለት ነበርና የልብሱ ስጦታ ከክርስቶስ የመጣ፣ በእናቱ እጅ ለታማኙ አገልጋይ የተሰጠ ሰማያዊ ሽልማት ኾኖ ይታያል። ምክንያቱም ቅዱስ ደቅስዮስ የምስጋና ቃላትን በድርሰቱ ሲያለብሳት እርሷ ደግሞ ሰማያዊ ልብስን አልብሳዋለች።
በሥዕሉ ላይ አበባ ይዞ ሲያበሥራት የሚታየው የመልአኩን ሰላምታ ለአንድ ጊዜ ብቻ ማቅረብ አንድ የውዳሴ አበባ እንደ ማቅረብ፣ ኅምሳ ጊዜ የመልአኩን ሰላምታ መጸለይ አንድ የአበባ ዕቅፍ ለእመቤታችን እንደ ማቅረብ፣ መቶ ኅምሳ (3 × 50 = 150) ጊዜ ማቅረብ መቶ ኅምሳ "ማሕሌተ ጽጌ" የጸሎት አበቦችን አንድ በአንድ ጐንጒኖ፣ ለድንግል ማርያም መንፈሳዊ አክሊል እንደ ማቅረብ ይመሰላል።
በዚኽ መጽሐፍ ደቅስዮስ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያመሰገነባቸው 24ቱ የአክሊል ክፍሎች ሲኖሩ፣ በተፈጥሮ ይዘታቸው በ3 ዋና ዋና ምድቦች ተከፍለዋል። እያንዳንዱ ዕንቁ፣ ኮከብና አበባ የእመቤታችንን ንጽሕና፣ ዘላለማዊ ድንግልና፣ ቅድስና፣ ትሕትና እና ለሰው ልጆች ያላትን ፍቅርና አማላጅነት የሚወክሉ መንፈሳዊ ምስጢራት አሏቸው።
Hoi! Ik ben Libroamiko, je boekadviseur.
Hoe kan ik je helpen?